BAKHC
ገጽታ
ቀለም
ዳራ
ወደ ዜናዎች እና ዝግጅቶች ተመለስ
ኩነት

የጠዋት የሰንበት ትምህርት — ለወጣቶች እና አዋቂዎች

ኖቬምበር 21, 2026 37 እይታዎች
ኖቬም
22
2026
እሑድ, ኖቬምበር 22 · 08:00
የጠዋት የሰንበት ትምህርት — ለወጣቶች እና አዋቂዎች

የጠዋት የሰንበት ትምህርት – ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች


በእምነት ማደግ እና በክርስቲያናዊ ምግባር እና መሪነት ትኩረት ያደረገት ምህርት


ስለፕሮግራሙ


የጠዋት የሰንበት ትምህርት ወጣቶችና አዋቂዎች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠናክሩ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት እንዲረዱ እና እምነታቸውን በዕለት ተዕለት ኑሯቸው እንዲተገብሩ የተዘጋጀ ሳምንታዊ መንፈሳዊ የትምህርት ነው።


ተሳታፊዎች በአንድነት የእግዚአብሔርን ቃል የሚማሩበት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች የሚያጠኑበት፣ ጥያቄዎችን የሚያነሱበት፣ የግል ምስክርነቶቻቸውንና የሕይወት ልምዶቻቸውን የሚካፈሉበት እና ተሳትፎን የሚያበረታታ መንፈሳዊ

የትምህርት ጊዜ ነው።


የፕሮግራሙ ዓላማ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀትን ከማሳደግ በላይ ጠንካራ የክርስትና መሠረት መገንባት፣ ክርስቲያናዊ ባሕርይን ማዳበር እና ተሳታፊዎች በቤተሰባቸው፣ በማኅበረሰባቸው፣ በሥራ ቦታቸውና በአጠቃላይ በሕይወታቸው ውስጥ የክርስቶስ ንቁ ተከታዮች እንዲሆኑ ማበረታታት ነው።


በፕሮግራሙ የሚካተቱ ዋና ዋና ትምህርቶች


1. የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና ግንዛቤ

የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት ማጥናት፣ በቡድን መወያየትና የተማርነውን ትምህርት በዕለት ተዕለት ኑሯችን እንዴት መተግበር እንደምንችል መረዳት።


2. መንፈሳዊ እድገትና የእምነት ግንባታ

ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ማጠናከር፣ በጸሎት ማደግ፣ መንፈሳዊ ሥርዓትን ማዳበርና በተለያዩ የሕይወት ፈተናዎች ውስጥ በእምነት ጸንቶ መቆምን መማር።


3. ምስክርነትና የሕይወት ልምድ ልውውጥ

በክርስቶስ ያለንን የግል ምስክርነት፣ ልምድ፣ ፈተናና የተማርናቸውን ትምህርቶች መካፈል። በራሳችን ልምድ ሌሎችን ማበረታታትና ከሌሎችም ልምድ መማር።


4. ክርስቲያናዊ ሕብረትና ወንድማማችነት

በፍቅር፣ በአንድነት፣ በመተባበርና በመደጋገፍ የተመሠረተ ጠንካራ የክርስቲያናዊ ሕብረት መገንባት። እርስ በርስ በመበረታታት በክርስቶስ አንድ ቤተሰብ ሆነን ማደግ።


5. የመሪነትና የግል እድገት ስልጠና

ክርስቲያናዊ የመሪነት ባሕርያትን ማዳበር፣ እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋና ስጦታ ማወቅ፣ ሌሎችን በትሕትና፣ በኃላፊነት፣ በታማኝነትና በዓላማ ማገልገልን መማር።


ማን መሳተፍ ይችላል?

ይህ ፕሮግራም በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ማደግ፣ የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት መረዳት፣ እምነታቸውን ማጠናከርና በክርስቲያናዊ ኑሮና አገልግሎት የበለጠ ውጤታማ መሆን ለሚፈልጉ ሁሉ ክፍት ነው።

በመንፈሳዊ ጉዞ ገና ለጀመራችሁም ሆነ ለብዙ ዓመታት ከክርስቶስ ጋር ለተጓዛችሁ፣ ለመማር፣ ለማደግና ለመበረታታት ሁልጊዜ አዲስ ዕድል አለ።


እንገናኝ!

የእሁድ ጠዋታችንን በትምህርት፣ በሕብረትና በመንፈሳዊ መታደስ የተሞላ ጊዜ እናድርገው። ለመማር በተዘጋጀ ልብና በክርስቶስ ለማደግ ባለ ፍላጎት ኑ።


ቀን፦ በየእሁዱ

ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:00 – 3:30

ተሳታፊዎች፦ ወጣቶችና አዋቂዎች


በቃሉ አብረን እናድግ፣ በእምነት እርስ በርስ እንበረታታ፣ እግዚአብሔር እንድንሆን የጠራን መሪዎችም እንሁን።


ተጨማሪ ለማንበብ

🧾 የባንክ ደረሰኝዎን ይላኩ
በባንክ ዝውውር ወይም በቴሌብር ሰጥተዋል? ቤተክርስቲያኗ እንድትመዘግበው ስክሪንሾቱን ይላኩልን። እናመሰግናለን!